Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ ወደ ካዛብላንካ ሞሮኮ የጭነት በረራ አገልግሎት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ ወደ ካዛብላንካ ሞሮኮ አዲስ የጭነት በረራ አገልግሎት መጀመሩን ገለጸ፡፡

አዲሱ አገልግሎት የሰሜን አፍሪካ መግሪብ ቀጣና ወደ ዓለም አቀፉ የጭነት አገልግሎት መዳረሻዎች ያካተተ አዲስ ምዕራፍ መሆኑንም የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ ዋና ሥራ አሥፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ገልጸዋል።

ዋና ስራ አስፈጻሚው የበረራው መጀመር በአፍሪካ ያለንን የዕቃ ጭነት መዳረሻ ቁጥር 35 አድርሶታል ማለታቸውን ከዓየር መንገዱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በተመሳሳይ ዓየር መንገዱ በእቃ ጭነት አገልግሎት ዘርፍ አስተማማኝ እና ቀልጣፋ አገልግሎት ለማቅረብ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያረጋግጥ መሆኑም ተመላክቷል፡፡

የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ በጭነት በረራ መዳረሻዎች ብዛት ከአፍሪካ ቀዳሚ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡

በዓለም የዓየር የዕቃ ጭነት አገልግሎት መስክ ቁልፍ ሚና እየተጫወተ ይገኛልም ነው የተባለው፡፡

የዓለም የንግድ እና የሸቀጦች ፍሰትን ለማሳለጥም አዳዲስ የጭነት መስመሮችን በመክፈት አገልግሎቱን በዓለም ዙሪያ ማስፋፋቱን እንደሚቀጥል ዓየር መንገዱ በመረጃው ጠቅሷል።

ወደ ካዛብላንካ የሚደረገው የጭነት በረራ በዘመናዊ እና ከ100 ቶን በላይ የመሸከም አቅም ባለው ቦይንግ 777-200ኤፍ የእቃ ጭነት አውሮፕላን እንደሚሆንም ተገልጿል፡፡

ዓየር መንገዱ በአሁኑ ጊዜ በአፍሪካ ያሉትን የጭነት መዳረሻዎች ብዛት ወደ 35 አሳድጓል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.