የአላስካ አየር መንገድ አደጋን ተከትሎ በርካታ ሀገራት የቦይንግ አውሮፕላኖች እንዳይበሩ አገዱ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአላስካ አየር መንገድ አደጋን ተከትሎ በተፈጠረ የደህንነት ስጋት በርካታ ሀገራት የቦይንግ አውሮፕላኖች በረራ እንዳያደርጉ ክልከላ ማድረጋቸው ተገለጸ፡፡
የአሜሪካ ፌዴራል አቪዬሽን አስተዳደር (ኤፍኤኤ) ትናንት ባወጣው መግለጫ ኤጄንሲው ደህንነታቸው በተጠበቀ መልኩ መስራት እንደሚችሉ እስኪያረጋግጥ ድረስ በአጠቃላይ 171 ቦይንግ ማክስ 9 አውሮፕላኖች ከበረራ መታገዳቸውን አስታውቋል።
በአሜሪካ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ አንዳንድ ቦይንግ 737 ማክስ 9 አውሮፕላኖች በጊዜያዊነት በረራ እንዲያቆሙ መደረጉም ተመላክቷል፡፡
ውሳኔው የተላለፈው ባለፈው ዓርብ ከፖርትላንድ ወደ ኦሪገን በረራ ላይ የነበረው የአላስካ አየር መንገድ የቦይንግ 737 ማክስ 9 አውሮፕላን ዋና ክፍል ላይ ችግር መከሰቱን ተከትሎ ነው።
አደጋው የተከሰተው አውሮፕላኑ አገልግሎት ላይ በዋለ በስምንት ሳምንታት ቆይታ ውስጥ መሆኑ ተገልጿል።
የኤፍኤኤ አስተዳዳሪ ማይክ ዊትከር እንዳሉት፤ የተወሰኑ ቦይንግ 737 ማክስ 9 አውሮፕላኖች ወደ በረራ ከመመለሳቸው በፊት አፋጣኝ ፍተሻ ያስፈልጋል።
ለውሳኔ እንዲረዳም ብሔራዊ የትራንስፖርት ደህንነትን በማገዝ በአላስካ አየር መንገድ በረራ 1282 ላይ የሚደርገው ምርመራ እንደሚቀጥል መናገራቸውን ሲጂቲኤን ዘግቧል።
ቦይንግ በዓለም አቀፍ ደረጃ በአጠቃላይ 218 ማክስ 9 አውሮፕላኖችን ያስረከበ ሲሆን አሁን ላይ የኤፍኤኤ የአደጋ ጊዜ የአየር ብቃት መመሪያው 171 የሚጠጉ አውሮፕላኖችን ሊመለከት እንደሚችል ማይክ ዊትከር ተናግረዋል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!