አንድ አዛውንት ከመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ በኋላ ከፍርስራሽ ውስጥ በሕይወት ተገኙ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አንድ በ90ዎቹ የዕድሜ ክልል የሚገኙ ሴት አዛውንት በምዕራብ ጃፓን ከደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ በኋላ በሕይወት መገኘታቸው ተሰምቷል፡፡
የዕድሜ ባለጸጋዋ 124 ሠዓታትን በፍርስራሽ ውስጥ ከቆዩ በኋላ ነው በሕይወት መገኘታቸው የተገለጸው፡፡
ሴትዮዋ የተገኙበት አካባቢ በሬክተር ስኬል 7 ነጥብ 6 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ መከሰቱን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡
በአደጋው ቢያንስ የ126 ሰዎች ሕይወት ማለፉንም ዘገባው አመላክቷል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!