Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል 10 ሚሊየን የአቮካዶ ችግኝ እየተዘጋጀ ነው

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሠ-መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በክልል ሁሉም ዞኖች 10 ሚሊየን የአቮካዶ ችግኝ እንክብካቤ አየተደረገለት እንደሚገኝ ገለጹ፡፡

ርዕሠ-መስተዳድሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ እስካለፈው ክረምት ከ16 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በውጭ ገበያ ተፈላጊ በሆነ የአቮካዶ ዝርያ መሸፈኑን አመላክተዋል፡፡

በሚቀጥለው ክረምት ይህንን ቁጥር ከእጥፍ በላይ ለመጨመር እየሰራን እንገኛለንም ብለዋል፡፡

በዚህም 25 ሺህ ሄክታር መሬት በአቮካዶ በመሸፈን፣ የምርጥ ዘር አቮካዶ ጠቅላላ ሽፋን 40 ሺህ ሄክታር ለማድረስ እየተሰራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡

በግብርናው ሴክተር ለማሳካት ከተያዙ ዋና ዋና ዓላማዎች አንዱ ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ የግብርና ምርቶችን ማስፋት መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ላለፉት 5 አመታት በክልሉ ሲተገበር የነበረው የምርጥ ዘር አቮካዶ ኢኒሼቲቭ ከዚህ አላማ የሚመነጭ መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡

በቀጣይም ሁሉም ባለድርሻ አካላት በተገኘው ስኬት ሳይዘናጋ በበለጠ ትኩረትና ተነሳሽነት እንዲሠራ አስገንዝበዋል።

ከስኬቱ ጀርባ ላሉ አርሶ አደሮችና የግብርና ባለሙያዎችም ያላቸውን አክብሮትና ምስጋና ገልጸዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.