ተመድ በ2024 የዓለም ምጣኔ ሀብት እድገት ወደ 2 ነጥብ 4 በመቶ ዝቅ እንደሚል ተነበየ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) በፈረንጆቹ 2024 የዓለም ምጣኔ ሀብት እድገት ወደ 2 ነጥብ 4 በመቶ ዝቅ እንደሚል ትንቢቱን አስቀምጧል።
ተመድ ትንበያውን ይፋ ያደረገው በፈረንጆቹ 2024 የዓለም ምጣኔ ሀብት ሁኔታ እና ተስፋ በሚል ርዕስ ባቀረበው ሪፖርት መሆኑ ተመላክቷል፡፡
እንደ ሪፖርቱ የዓለም ምጣኔ ሀብት በፈረንጆቹ 2023 ታቅዶ ከነበረው 2 ነጥብ 7 በመቶ ዕድገት በተያዘው የፈረንጆቹ 2024 ወደ 2 ነጥብ 4 ዝቅ እንደሚል አሳይቷል፡፡
ይህም በኮሮና ወረርሽኝ ወቅት ከነበረው የዕድገት ምጣኔ በ3 በመቶ ያነሰ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
በተመድ የምጣኔ ሀብትና ማህበራዊ ደህንነት ዘርፍ የምጣኔ ሀብት ትንተናና ፖሊሲ ክፍል ዳይሬክተር ሃንታኑ ሙከርጂ ዓለም 3 በመቶ ምጣኔ ሀብታዊ ዕድገት ለማስመዝገብ እየታገልች ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በፈረንጆቹ 2024 ዓለም አቀፍ አማካይ የግሽበት መጠን 3 ነጥብ 9 በመቶ እንደሚሆንም ሙከርጂ ማብራራታቸው ተገልጿል፡፡
ይህም በፈረንጆቹ 2022 ታይቶ ከነበረው የ 8 ነጥብ 1 በመቶ አንፃር ፈጣን ለውጥ ነው ሲሉም አክለዋል፡፡
በታዳጊ ሀገራት የዓመቱ የግሽበት መጠንም ከ10 በመቶ በላይ እንደሚሆንም አያይዘው መግለፃቸውን ዘ ኬብል ዘግቧል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!