Fana: At a Speed of Life!

በጃፓን በአውሮፕላን አደጋ ምክንያት ከ100 በላይ በረራዎች ተሰረዙ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጃፓኗ ቶኪዮ ከተማ የተከሰተውን የአውሮፕላን አደጋ ተከትሎ ከ100 በላይ በረራዎች መሰረዛቸውን የጃፓን አየር መንገድ አስታወቀ፡፡

በሰሜናዊ ጃፓን ከምትገኘው ሳፖሮ ከተማ ወደ ቶኪዮ ከተማ እየበረረ የነበረው የመንገደኞች አውሮፕላን በቶኪዮ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ እርዳታ እየሰጠ ከነበረ አውሮፕላን ጋር ተጋጭቶ የአምስት ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡

በሁለተኛው የእርዳታ ሰጭ አውሮፕላን ውስጥ የነበሩ አምስት የበረራ ቡድን አባላትም ህይወታቸው ማለፉን የጃፓን የትራንስፖርት ሚኒስትር ቴሱሶ ሳይቶ ገልፀዋል፡፡

አደጋውን ተከትሎም በጃፓን በዛሬው እለት ሊደረጉ የነበሩ ከ100 በላይ የሃገር ውስጥና ዓለም አቀፍ በረራዎች መቋረጣቸው ተሰምቷል፡፡

በዚህም የአየር መንገዱ ተጠቃሚ የነበሩ 20 ሺህ በላይ ደንበኞች ጉዞ መስተጓጎሉ ነው የተሰማው።

በሀገሪቱ የተከሰተውን በረራ ለማካካስ የጃፓን መንግስት የባቡር ትራንስፖርት አማራጭ ማቅረቡን ሲ ኤን ኤን ዘግቧል።

ትራንስፖርቱ እንዳይስተጓጎል የማዕከላዊ ጃፓን ባቡር ጣቢያ ተጨማሪ የትራንስፖርት ባቡሮችን አግልገሎት ላይ አውሏልም ተብሏል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.