ከፍተኛ የሃማስ ባለሥልጣን መገደሉ ተሰማ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሳሌህ አል አሮሪ የተባለ የሃማስ ከፍተኛ ባለሥልጣን በቤይሩት በደረሰ ፍንዳታ መገደሉ ተገለጸ፡፡
አል አሮሪ ÷ የአንድ የሃማስ ወታደራዊ ክንፍ መሥራች እና የቡድኑ የፖለቲካ ቢሮ ምክትል መሪ እንደነበር ስካይ ኒውስ አስነብቧል፡፡
አል አሮሪ በዌስት ባንክ ሃማስን ማገልገሉም ነው የተነገረው፡፡
የሊባኖስ መንግሥት ብሔራዊ የዜና አገልግሎት እንደገለጸው ÷ በፍንዳታው የአራት ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ ፤ በድሮን እንደተመታም አያይዞ ጠቁሟል፡፡
ሃማስ በከፍተኛ አመራሩ ላይ ለተፈጸመውን ግድያ እስራዔልን ተጠያቂ ማድረጉም ነው የተገለጸው፡፡