Fana: At a Speed of Life!

በጃፓን በተከሰተ ርዕደ መሬት የሟቾች ቁጥር 30 መድረሱ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጃፓን በተከሰተ ርዕደ መሬት በትንሹ 30 ሰዎች ህይወታቸውን ማጣታቸው ተገልጿል፡፡
 
ወደ 1 ሺህ የሚጠጉ የነፍስ አድን ሰራተኞች በፍርስራሽ ውስጥ የታፈኑ ሰዎችን በህይወት ለማዳን እየሰሩ መሆኑ ተገልጿል።
 
በጃፓን በትናንትናው እለት ለዜጎች ተሰጥቶ የነበረው የማዕበል (ሱናሚ) ስጋት በዛሬው ዕለት ቢነሳም በርዕደ መሬቱ የሚደርሰው ጉዳት ሊጨምር እንደሚችል ስጋት አለ ነው የተባለው።
የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሺዳ ርዕደ መሬቱ በርካታ ጉዳቶችን አስከትሏል ብለዋል።
 
የጃፓን ጦር ከቤት ለመፈናቀል ለተገደዱ ሰዎች ምግብ፣ ውሃ እና ብርድ ልብስ ጨምሮ የተለያዩ ግብዓቶችን እያቀረበ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል።
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ሀገራቸው ማንኛውንም አስፈላጊ እርዳታ ለመስጠት ዝግጁ ስለመሆኗ ተናግረዋል።
 
አደጋው የባህር ዳርቻ ከተማ በሆነችው ሱዙ በ1 ሺህ ቤቶች ላይ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን የከተማው ከንቲባ ማሱሂሮ ኢዙሚያ ክስተቱን “አሰቃቂ” ሲሉ ገልጸውታል።
 
በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት ርዕደ መሬት የተከሰተበት የባህር ዳርቻ ከተማ ሱዙ 5 ሺህ አባወራዎች ብቻ እንደሚኖሩበት ተመላክቷል።
 
 
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC(Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.