አቶ ሽመልስ አብዲሳ ኢትዮጵያ የባሕር በር የምታገኝበትን የመግባቢያ ሥምምነት በመፈረሟ የተሰማቸው ደስታ ገለጹ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ኢትዮጵያ የባሕር በር የምታገኝበትን የመግባቢያ ሥምምነት ከሶማሌ ላንድ ጋር በመፈራረሟ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ የባሕር በር የምታገኝበትን የመግባቢያ ሥምምነት ከሶማሌ ላንድ ጋር በዛሬው ዕለት ተፈራርማለች።
ስምምነቱንም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የሶማሌላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ በአዲስ አበባ ተፈራርመዋል፡፡
ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ ጉዳዩን አስመልክተው በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ ኢትዮጵያ የባሕር በር የምታገኝበትን የመግባቢያ ሥምምነት በመፈረሟ ለኦሮሞ ሕዝብና ለመላው ኢትዮጵያውያን እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡