Fana: At a Speed of Life!

የሩሲያ ጠላት ዩክሬን ሳትሆን ከጀርባዋ ያሉት ናቸው – ፕሬዚዳንት ፑቲን

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያ ጠላት ዩክሬን ሳትሆን ከጀርባዋ ያሉት ምዕራባውያን ናቸው ሲሉ የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ተናገሩ፡፡

ፕሬዚዳንቱ በሞስኮ ወታደራዊ ሆስፒታል ተገኝተው በሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት የተጎዱ ወታደሮችን ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝቱ ወቅት ፕሬዚዳንት ፑቲን÷ ምዕራባውያን ዩክሬንን ተጠቅመው ሩሲያን እየወጉ ነው፣ እውነተኛ ጠላታችን ዩክሬን ሳትሆን የምዕራባውያን ፖለቲከኞች ናቸው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ምዕራባውያን ጠላታችን የሆኑት ለዩክሬን ወታደራዊ ድጋፍ በማድረጋቸው ሳይሆን ዩክሬንን በመጠቀም ፖለቲካዊ ፍላጎታቸውን ለማሳካት እየሰሩ ስለሆነ ነው ብለዋል፡፡

ሞስኮ እና ኬቭ ጦርነት ውስጥ የገቡት በምዕራባውያን በተቀናበረ ሴራ እና ሩሲያን ማሸነፍ በሚፈልጉ ሀይሎች ምክንያት መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

ሆኖም ምዕራባውያን ሩሲያን ለማንበረክክ ያቀዱት ሴራ አልተሳካለቸውም ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ ምዕራባውያን ትናንት ሩሲያን በቀላሉ እንዴት እንደሚያሸንፉ ሲያቅዱ ነበር አሁን ላይ ግን ከማሸነፍ ይልቅ ጦርነቱን ስለማቆም እየመከሩ ነው ብለዋል፡፡

ለዘላለም ስንዋጋ አንኖርም ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ ሩሲያ ጥቅሟን ባስከበረ መልኩ ጦርነቱን ለማቆም ዝግጁ እንደሆነች መግለጻቸውን አር ቲ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.