ስፔን የኒውክሌር ማብላያ ማዕከሎቿን በ2035 ለመዝጋት ማቀዷን ገለጸች
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ስፔን የኒውክሌር ሃይል ማብላያ ማዕከሎቿን በፈረንጆቹ 2035 ለመዝጋት ማቀዷን አስታውቃለች፡፡
ሀገሪቷ የኒውክሌር ማብላያ ማዕከሎቿን ለመዝጋት ያቀደቸው በታዳሽ ሃይል ዘርፍ ላይ በትኩረት ለመስራት በማለም መሆኑ ተመላክቷል፡፡
ይሁን እንጂ እቅዱ ስፔን በርካታ ሃይል የምታገኝበትን የኒውክሌር ቴክኖሎጂ ያሳጣታል በሚል በበርካቶች ትችት እንደቀረበበት አርቲ በዘገባው አስፍሯል፡፡
በስፔን ተፎካካሪ ፓርቲ የሆነው ወግ አጥባቂ ፓርቲ ማዕከላቱን ለመዝጋት የተወሰነውን ውሳኔ ለመቀልበስ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትብር እንደሚሰራ አስታውቋል፡፡
ፖለቲካ እና ርዕዮተ ዓለም በሀገሪቱ በተዘረጋው የኒውክሌር መሰረት ልማትላይ ተጽዕኖ ማሳደር እንደሌለበትም ተጠቁሟል፡፡
የኒውክሌር ማብላያ ማዕከላቱን ለማስወገድ 22 ነጥብ 3 ሚሊየን ዶላር በላይ የሚያስፈልግ ሲሆን ÷ይህም በተቋማቱ እንደሚሸፈን ተገልጿል፡፡
በአውሮፓ ሀገራት ከስፔን በተጨማሪ ጀርመን የኒውክሌር ማብላያ ተቋማትን መዝጋት መጀመሯ በዘገባው ተመላክቷል፡፡