በእንስሳት በሚፈጸም ጥፋት የተሽከርካሪ ብልሽት መጠን ጨምሯል ተባለ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንስሳት አማካኝነት የሚደርስ የተሽከርካሪ ብልሽት ከፍተኛ ደረጃ የደረሰ ሲሆን÷ ለአብዛኞቹ ጥፋቶችም አይጦች ተጠያቂ ናቸው ተብሏል።
ሮያል አውቶሞቢል ክለብ (አርኤሲ) የተሰኘው ድርጅት÷ በ2023 የመጀመሪያዎቹ 11 ወራት ውስጥ 303 ተሽከርካሪዎች በእንስሳት ጉዳት እንደደረሰባቸው ገልጿል፡፡
ይህም በፈረንጆቹ 2018 ከተመዘገቡት ክስተቶች ጋር ሲነፃፀር የ55 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን አመላክቷል።
በዚህ ዓመት በእንሰሳት ከተፈፀሙ ብልሽቶች ከግማሽ በላይ የሚሆኑት በአይጦች እንደተከሰቱና በአብዛኛውም የነዳጅ ቱቦዎችን መቀርጠፍ፣ የሞተር ቤትን መውረር እና የፊት መብራቶችን መስበር ይገኙበታል ብሏል።
ቀበሮዎች የፍጥነት መቆጣጠሪያ ሽቦዎችን፣ የመስታወት መጥረጊያዎችን እና የፍሬን ቱቦዎችን በማኘክ ጥፋት እንደሚያደርሱም ተገልጿል።
መኪናው አልነሳ ብሎት ተቸግሮ የነበረው በደቡብ ምዕራብ እንግሊዝ የአርኤሲ አባል ኒክ አይዛክ፤ ሽኮኮ የመኪናውን አየር ማጣሪያ የለውዝ ማጠራቀሚያ አድርጋው ማግኘቱን ተናግሯል።
የአርኤሲ ቃል አቀባይ አሊስ ሲምፕሰን እንስሳት በተለይም አይጦች መኪና ውስጥ ከገቡ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርሱ ስለሚችሉ መኪናን ለአንድ ሳምንት ወይም ከዚያ በላይ ሳያሽከረክሩ ከቆዩ በሚገባ መፈተሸ ተገቢ ነው ይላሉ፡፡
ከሁሉም በላይ በጣም ጠቃሚው ምክር ግን ምንም ዓይነት ምግብ መኪና ውስጥ እንዳልተተወ ማረጋገጥ ነው ማለታቸውን ስካይ ኒውስ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!