Fana: At a Speed of Life!

333 ኢትዮጵያን በመጀመሪያው ዙር ዛሬ ከቤሩት ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

365 ኢትዮጵያን በመጀመሪያው ዙር ዛሬ ከቤሂሩት ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤሩት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 333 ኢትዮጵያን ዛሬ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ።

የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ እና የሰላም ሚኒስቴሮች በጋራ በመሆን ነው ኢትዮጵያውያኑ ወደሀገራቸው እንዲመለሱ ያደረጉት።

ኢትዮጵያውያኑ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ጽዮን ተክሉ፣ የሰላም ሚኒስትር ዴአታ ወይዘሮ ፍሬዓለም ሽባባው፣ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ አየለች እሸቴ፣ የዳያስፖራ ኤጄንሲ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት አካላት ተገኝተው አቀባባል አድርገውላቸዋል።

ዛሬ ለሀገራቸው የበቁት እነዚህ ኢትዮጵያውያን በለይቶ ማቆያ ውስጥ እንደሚቆዩም ነው የተገለጸው።

በመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ካላቸው የስራ ባህሪ አንጻር በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ስራ በማቆማቸው ለተለያዩ ችግሮች መጋለጣቸው ይታወቃል።

በመሆኑም የዓለም አቀፍ ተቋማትን ስጋት እና ማሳሰቢያ እንዲሁም የዜጎቻችን ከአቅም በላይ በሆነ ተጋላጭነት ምክንያት ከሚኖሩበት ሀገር ወደ ሀገራቸው የመመለስ ከፍተኛ ፍላጎት ከግምት ውስጥ በማስገባት እየተሰራ ይገኛል ነው የተባለው።

በዚህም ዜጎች ክብራቸው ተጠብቆ ወደ ሀገር ቤት እንዲመለሱ ለማድረግ በኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ጽዮን ተክሉ የሚመራ 11 አባላት ያሉት ኮሚቴ ተቋቁሞ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተቋቁመውና በሰላም ሚኒስቴር ከሚመራው ግብረ ሃይል ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑ ይታወቃል።

በዚህም ሲደረግ የነበረው አስፈላጊው ዝግጅት በመጠናቀቁ ዛሬ 333 ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ከሊባኖስ እንዲመለሱ ተደርጓል።

በቀጣዩ ቅዳሜም 320 ኢትዮጵያዊያን ዜጎቻችን ከሊባኖስ ወደ አገራቸው ይገባሉ ተብሏል።

ባለፈው ግንቦት 13 ቀን 2012 ዓ.ም በተባበሩት ዓረብ ኢምሪቶች በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ 57 ኢትዮጵያዊያን በራሳቸው ፈቃድ እንዲመለሱ መደረጉም ይታወሳል።

በቀጣይ ቀናቶች በተለያዩ የአረብ ሀገራት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ወደሀገራቸው የመመለሱ ስራ እንደሚከናወንም ነው የተመለከተው።

በለይኩን ዓለም

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.