Fana: At a Speed of Life!

የዓልሸባብ ከፍተኛ አመራር ማኣሊም አይማን መገደሉ ተሰማ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሸባሪው ዓልሸባብ ከፍተኛ አመራር ማኣሊም አይማን በአሜሪካ ኃይሎች ድጋፍ የሶማሊያ ጦር ባካሄደው  ዘመቻ መገደሉ ተሰምቷል፡፡

ማኣሊም አይማን በሶማሊያና በአካባቢው ሀገራት የተለያዩ የሽብር ጥቃቶችን በመምራት አስፈጽሟል በሚል ሲታደን መቆየቱ ይታወሳል፡፡

ሰውየው በተለይም ከሦስት ዓመታት በፊት በኬንያ ሰሜናዊ ድንበር ማንዳቤይ ወታደራዊ የዓየር ምድብ ላይ በመራው የሽብር ጥቃት ኬንያውያንና አሜሪካውያን ለኀልፈት መዳረጋቸው ይታወቃል፡፡

አሜሪካ ይህን ሰው ያለበትን ለጠቆመ 10 ሚሊየን ዶላር ወሮታ እከፍላለሁ እስከማለትም ደርሳ ነበር።

ማኣሊም አይማን በጥምር በተካሄደ ዘመቻ ስለመገደሉ የሶማሊያ የማስታወቂያ ሚኒስትር ዳውድ አዌይስ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሠፈሩት ጽሑፍ አረጋግጠዋል ሲሉ ዓለም አቀፍ የዜና አውታሮች ዘግበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.