Fana: At a Speed of Life!

በኬንያ በደረሰ የጎርፍ አደጋ ከ174 ሰዎች በላይ ሕይወት ተቀጠፈ

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣስ 10 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኬንያ በደረሰ የጎርፍ አደጋ ከ174 በላይ ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡

እንደ ስፑትኒክ ዘገባ የጎርፍ አደጋው የተከሰተው በኤልኒኖ ተፅዕኖ ምክንያት በዘነበ ያልተለመደ የዝናብ መጠን መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በቅርቡ የተመዘገበው የሰዎች ኅልፈት የተከሰተው በመካከለኛው ኪያምቡ ግዛት መሆኑን ዘገባው አመላክቷል፡፡

ከዝናቡ ጋር በተያያዘ የመሬት መንሸራተት መከሰቱም ተገልጿል፡፡

በደቡብ ምዕራብ ሚጎሪም እንደዚሁ በወርቅ ማዕድን ማውጫ አካባቢ በተከሰተ የጎርፍ መጥለቅለቅ የሰዎች ሕይወት ማለፉ ተጠቁሟል፡፡

በርካታ የኬንያ ገጠራማ ክፍል መኖሪያ ቤቶች በጎርፍ መወሰዳቸውም ነው የተነገረው፡፡

በጎርፉ ምክንያት በርካታ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን እየጣሉ መሸሻቸውን ዓለምአቀፉ የቀይ መስቀልና ቀይ ጨረቃ ፌዴሬሽን መረጃ ያመላከተ ሲሆን የእርሻ ቦታዎችም በውሃ ተውጠዋል ነው የተባለው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.