Fana: At a Speed of Life!

እስራኤል ለሃማስ አዲስ የስምምነት ዕቅድ ማቅረቧ ተሰማ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሃማስ ታጣቂ ቡድን ተጨማሪ ታጋቾችን ከለቀቀ እስራኤል በጋዛ ሰርጥ የምታደርገውን ወታደራዊ እንቅስቃሴ ለአጭር ጊዜ ለማቆም ዝግጁ መሆኗን አር ቲ የእስራኤል መገናኛ ብዙሃንን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።
የስምምነት ሀሳቡ በኳታር አሸማጋዮች በኩል የቀረበ ሲሆን እስከ 40 የሚደርሱ ሴቶች፣ አረጋውያን እና ታማሚዎች ከእስር እንዲፈቱ ለሰባት ቀናት የሚቆይ የተኩስ አቁም እቅድ እንዳለው ተዘግቧል።
ሃማስ ጦርነቱ ሙሉ በሙሉ እንዲቆም እንደጠየቀና ነገር ግን ታጣቂ ቡድኑ ገለልተኛ እስኪሆን ድረስ ጦርነቱን ለመቀጠል ቃል የገባው የእስራኤል አመራር ጥያቄው ተቀባይነት የለውም ብሏል።
ቢያንስ ስምንት አሜሪካውያንን ጨምሮ 128 የእስራኤል እና የውጭ ሀገር ዜጎች አሁንም በጋዛ ታግተው እንደሚገኙ ይታመናል።
እስራኤል በምትለዋወጠው የፍልስጤም እስረኞች ቁጥር ልክ የተኩስ አቁም ቀናትን እንደአስፈላጊነቱ ለመወሰን ዝግጁ መሆኗም ተመላክቷል፡፡
ቀደም ሲል ለአንድ ሳምንት በዘለቀው የተኩስ አቁም ስምምነት ሃማስ 105 ታጋቾችን ሲፈታ በምትኩ በእስራኤል እስር ቤቶች የሚገኙ 240 ፍልስጤማውያን መለቀቃቸው ይታወሳል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.