Fana: At a Speed of Life!

የቀይ ባሕርን ደኅንነት ለማረጋገጥ ከ10 ሀገራት የተውጣጣ ኃይል መዋቀሩ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቀይ ባሕር ያለውን የንግድ ደኅንነት ለማረጋገጥ ከ10 ሀገራት የተውጣጣ ኃይል መዋቀሩን አሜሪካ አስታወቀች፡፡

የጸጥታ ኃይሉ የተዋቀረው የሁቲ አማፂያን በቀጣናው ተደጋጋሚ ጥቃት በማድረሳቸው እና የበርካታ ኩባንያዎች የመርከብ ጭነት አገልግሎት በመስተጓጎሉ መሆኑ ተነግሯል፡፡

የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስቲን እንደተናገሩት÷ ባሕሬን፣ ካናዳ፣ ፈረንሳይ፣ ጣሊያን፣ ሲሼልስ እና ብሪታኒያ ጥምር የደኅንነት ኃይል ኢኒሼቲቩን ከሚቀላቀሉት ሀገራት መካከል እንደሚገኙበት ተናግረዋል።

ነፃ የባሕር እንቅስቃሴን በተመለከተ የተቀመጡት መሠረታዊ መርሆች እንዳይጣሱ የሚፈልጉ ሀገራት መሥመሩን ከአማፂ ቡድኑ ለመጠበቅ በአንድነት መቆም አለባቸውም ብለዋል፡፡

የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር መግለጫውን ያወጣው ባሳለፍነው ሣምንት ከእንግሊዝ ባሕር ኃይል ጋር በመተባበር በቀይ ባሕር አካባቢ ሲያንዣብቡ የነበሩ 15 የጠላት ሰው አውሮፕላኖችን መትተን ጥለናል ማለታቸውን ተከትሎ መሆኑን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

አማፂ ቡድኑ እስራዔል በጋዛ እርምጃ መውሰድ ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ ከእስራዔል ጋር ግንኙነት አላቸው በሚላቸው ሀገራት የመርከብ ጭነቶች ላይ ያነጣጠረ በሚሳዔል እና በሰው አልባ አውሮፕላኖች የታገዘ እርምጃ እየወሰደ ነው፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.