Fana: At a Speed of Life!

ቲክ ቶክ የይዘት ፖሊሲውን የጣሱ ከ136 ሚሊዮን በላይ ቪዲዮዎችን ከገፁ ማውረዱን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይናው ኢንተርኔት ቴክኖሎጂ ኩባንያ ቤትዳንስ ይዞታ የሆነው ቲክ ቶክ ማህበራዊ ትስስር ገጽ በሩብ ዓመቱ ብቻ የይዘት ፖሊሲውን የጣሱ 136 ሚሊዮን በላይ ቪዲዮዎችን ከመተግበሪያው ማጥፋቱን አስታውቋል፡፡

ቲክ ቶክ እንዳስታወቀው÷ የይዘት ፖሊሲውን ከጣሱ 50 ሀገራት ናይጀሪያ ቀዳሚ ሰትሆን ከናይጀሪያውያን ተጠቃሚዎች ብቻ በሩብ ዓመቱ 1 ነጥብ 4 ሚሊዮን ተንቀሳቃሽ ምስሎች እንዲወርዱ ተደርጓል።

ኩባንያው የማህበረሰብ መመሪያዎችን ጥሰዋል ያላቸውን እነዚህ የ50 ሀገራት ተጠቃሚዎች 90 በመቶ የሚሆኑትን ተንቀሳቃሽ ምስሎች ከገፁ ላይ ማውረዱን አስታውቋል፡፡

የወረዱት ምስሎች ከታማኝነት እና ትክክለኛነት፣ ከግለኝነት እና የሳይበር ደህንነት፣ የእዕምሮ ጤና እና ማህበራዊ ደህንነትን ጨምሮ ሌሎች ተጨማሪ የቲክቶክ ፖሊሲዎችን የጣሱ መሆናቸው ተመላክቷል፡፡

ኩባንያው 73 ነጥብ 6 ሚሊዮን አካውንቶችን፣ 348 ሚሊዮን ላይኮችን፣ 211 ነጥብ 3 የውሸት ተከታዮችን እና 7 ነጥብ 2 ቢሊዮን የውሽት የጓደኝነት ጥያቄ አቅራቢዎችን ከገፁ ማስወገዱን አስታውቋል፡፡

በተጨማሪም ቲክቶክ የማስታወቂያ ህግን ጥሰዋል ያላቸውን 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ማስታወቂያዎችን ከገፁ ማውረዱን ገልጿል፡፡

ቲክ ቶክ ተመራጭ እና ተፅዕኖ ፈጣሪ ማህበራዊ ሚዲያ ሲሆን በቅርቡ ከዓለም አቀፍ ተጠቃሚዎች 10 ቢሊዮን ዶላር ገቢ አግኝቻለሁ ማለቱ ይታወሳል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.