የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል 240 ሚሊየን ብር ለዞኖች የፕሮጀክት ግንባታ ማስጀመሪያ እንዲሆን ወሰነ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በምስረታ በዓል ላይ ከሰበሰበው ሃብት 40 በመቶ የሚሆነው ለዞኖች እንዲወርድ መወሰኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ገለጹ፡፡
240 ሚሊየን ብር የሚሆነው ሃብት በዞኖች ለሚጀመር ፕሮጀክት ግንባታ መነሻ ካፒታል እንዲሆን ታስቦ መወሰኑን የክልሉ ኮሙኑኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
አቶ ጥላሁን ለፕሮጀክቱ ግንባታ ስኬታማነት የክልሉ ምክር ቤት አባላት አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምስረታ ህዳር 13 ቀን 2016 ዓ.ም ሲካሄድ የክልል መስተዳድሮችና የከተማ አስተዳደሮች ለክልሉ ያላቸውን አጋርነት ለመግለጽ ከ580 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጋቸው ይታወሳል።