Fana: At a Speed of Life!

በቻይና በደረሰ የባቡር አደጋ 515 ተሳፋሪዎች ላይ ጉዳት ደረሰባቸው

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቻይና በደረሰ የባቡር አደጋ 515 ተሳፋሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱ ተገለጸ፡፡

ጉዳት የደረሰባቸው ተሳፋሪዎች ወደ ሆስፒታል የተወሰዱ ሲሆን 102ቱ ላይ የአጥንት ሥብራት እንደደረሰባቸው ታይም አስነብቧል፡፡

ሁለት ተከታትለው ሲጓዙ በነበሩ ባቡሮች ላይ አደጋው የደረሰው በወቅቱ ከባድ በረዶ በመጣሉና ሐዲዱን ፍሬን ለመያዝ አሥቸጋሪ ስላደረገው መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ባቡሮቹ በተራራማው የቤጂንግ ምዕራብ ክፍል ሲጓዙ እንደነበረና ቁልቁለት ላይ የፊተኛው ባቡር ፍሬን ሲይዝ የኋለኛው በበረዶው ምክንያት ፍሬን መያዝ ስላልቻለ ተንሸራቶ በመላተሙ ጉዳቱ መድረሱን የከተማው የትራንስፖርት ባለሥልጣን ገልጿል፡፡

በወቅቱ የአደጋ ጊዜ የሕክምና ባለሙያዎች ፣ ፖሊስ እና የመንገድ ባለሥልጣናት ተረባርበው የሰዎችን ሕይወት መታደጋቸው ተጠቁሟል፡፡

25 ሰዎች በፅኑ የሕክምና ክፍል በክትትል ላይ ሲሆኑ 67ቱ ደግሞ ቀላል የሕክምና ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ተነግሯል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.