ሃማስ ላይ የምወስደው እርምጃ ወራት ሊወስድ ይችላል – እስራዔል
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሃማስን ለመደምሰስ ከጥቂት ወራት በላይ ሊወስድባቸው እንደሚችል የእስራዔል መከላከያ ሚኒስትር ዮአቭ ጋላንት አስታወቁ፡፡
ሚኒስትሩ ረጅም ጊዜ የሚወስድብን ጦርነት ይሆናል ማለታቸውን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡
እስራዔል በጀኒን ለ60 ሠዓታት ፈጽማዋለች በተባለ ደብድባ 11 ፍልሥጤማውያን ለህልፈት ከተዳረጉ በኋላ ተልዕኮዋን ማጠናቀቋ ተጠቁሟል፡፡
በሌላ በኩል ወታደራዊ ኃይሏ ቀደም ሲል በተቆጣጠረው ዌስት ባንክ ሌሊቱን ተጨማሪ ጥቃት መፈጸሙ ተነግሯል፡፡
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አሁንም እስራዔል “ንፁሐንን እንዴት ማትረፍ እንዳለባት” ትኩረት ማድረግ እንዳለባት አሳስበዋል ነው የተባለው።
እንደ ዘገባው ከሆነ በጦርነቱ ምክንያት አሁንም በጋዛ የግንኙነት መሥመሮች ተቋርጠዋል፡፡
መረጃዎች እንደሚያመላክቱት እስካሁን በፍልሥጤም የሟቾች ቁጥር ቢያንስ 18 ሺህ 787 ሲደርስ ከእስራዔል በኩል የ1 ሺህ 147 ሰዎች ሕይወት አልፏል ተብሏል፡፡