Fana: At a Speed of Life!

በሶፍትዌር ዕክል ምክንያት ከ2 ሚሊየን ለሚልቁ የቴስላ ምርቶች ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኤለን መስክ አንዱ ኩባንያ የሆነው“ቴስላ አውቶሞቲቭ” በሶፍትዌር ችግር ምክንያት ከ2 ሚሊየን የሚልቁ ተሸከርካሪዎቹን ለማዘመን ጥሪ ማቅረቡ ተሰምቷል፡፡

ጥሪ የቀረበው የአሜሪካው ቁጥጥር ባለሥልጣን ለሁለት ዓመታት ፍተሻ ሲያደርግ ቆይቶ የመኪናዎቹ የ”አውቶ ፓይለት” ሥርዓት ችግር እንዳለበት በማሳወቁ ምክንያት መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

መኪናዎቹ የተገጠመላቸው የ“ድራይቨር አሲስታንስ” ቴክኖሎጂ ሥርዓት (“አውቶፓይለት”) ሾፌሩን የሚያግዝ ክፍል በከፊል ጉድለት እንዳለበት የባለሥልጣኑ የምርመራ ውጤት አረጋግጧል።

በመሆኑም ከፈረንጆቹ 2015 ጀምሮ በአሜሪካ የሚንቀሳቀሱ የ“አውቶ ፓይለት ሥርዓት” የተካተተላቸው ከ2 ሚሊየን የሚልቁ መኪናዎች የሶፍትዌር ዝመና እንዲደረግላቸው ኩባንያው ጥሪ ማቅረቡን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ኩባንያው ጉዳዩ ቀላል እንደሆነና የመኪናዎቹን ሶፍትዌር ባሉበት በማዘመን ብቻ በአጭር ጊዜ እንደሚፈታ አስታውቋል፡፡

ደንበኞቹ ሶፍትዌራቸውን ለማዘመን ወይም “አፕዴት” ለማድረግ ወደ ኩባንያው ወይም ወደ ቴስላ የሽያጭ ማዕከላት መሄድ እንደማያስፈልጋቸው ባሉበት ሶፍትዌሩን “አፕዴት” በማድረግ ብቻ ችግራቸው እንደሚፈታም አስታውቋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.