Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ በዶሃ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የንግድ እና ኢንቨስትመንት መድረክ በኳታር ዶሃ ተካሄደ፡፡

መድረኩ ኢትዮጵያና ኳታር በአበባ ንግድ እንዲሁም በዘመናዊ ግብርና እና ቱሪዝም ያላቸውን ምጣኔ ሐብታዊ ትብብር ለማጠናከር ያለመ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ጉባዔው ኳታር በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስተባባሪነት የተዘጋጀ ሲሆን÷ የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ምሥጋኑ አርጋ እንደታደሙበት ተመልክቷል፡፡

በመድረኩ የግብርና ሚኒስትር ዴዔታ ሶፊያ ካሳ (ዶ/ር)፣ የንግድና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስትር ዴዔታ አቶ ካሳሁን ጎፌ፣ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሌሊሴ ነሜ እንደሳተፉም ተገልጿል፡፡

በኳታር የኢትዮጵያ አምባሳደር ፈይሰል አሊ እና የዶሃ ኤክስፖ ኮሚሽነር ጀነራል አምባሳደር ባደር ቢን ኦማር አል ዳፋ የመድረኩ ተሳታፊዎች ናቸው፡፡

የኳታር ኢንተርፕራይዞች እና በኳታር የሚኖሩ የኢትዮጵያ ማኅበረሰቦች በጉባዔው መሳተፋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በኢትዮጵያ በአትክልትና ፍራፍሬ ፣ ቡና ፣ ቱሪዝም እንዲሁም በሌሎች መሠል የልማት ዘርፎች ዕምቅ የመልማት ዐቅም መኖሩን የጠቀሱት አምባሳደር ምሥጋኑ፤ የኳታር አልሚዎች በኢትዮጵያ መዋዕለ-ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በኳታር የኢትዮጵያ አምባሳደር ፈይሰል አሊ በበኩላቸው፤ በግብርና፣ አየር በረራ፣ ቱሪዝም እና የሀይል ልማት ዘርፎች ሁለቱ ሀገራት ያላቸውን ንግድና ኢንቨስትመንትን ማጠናከር እንዳለባቸው መግለጻቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.