Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የሠላም ማስከበር ተልዕኮ ያላትን አስተዋፅዖ አጠናክራ እንደምትቀጥል ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 28 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የሠላም ማስከበር ተልዕኮ ያላትን የጎላ አስተዋፅዖ አጠናክራ እንደምትቀጥል የመከላከያ የሠላም ማስከበር ማዕከል አዛዥ ሜጀር ጄኔራል አዳምነህ መንግሥቴ ተናገሩ።

የዓለም አቀፍ ሠላም ማስከበር ማሠልጠኛ ኢንስቲትዩት፥ አጋርነትን በተመለከተ ተቀማጭነታቸው አዲስ አበባ ከሆነ የተለያዩ ሀገራት ወታደራዊ አታሼዎች ጋር ተወያይቷል።

የመከላከያ የሠላም ማስከበር ማዕከል አዛዥ ሜጀር ጄኔራል አዳምነህ መንግሥቴ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት ÷ ኢትዮጵያ በዓለም የሠላም ማስከበር ተልዕኮ ዓርአያ የሚሆኑ ተግባራትን አከናውናለች።

ከዚህ የላቀ አፈጻጸም ለማስመዝገብም መከላከያ በጠንካራ ሪፎርም የተደገፈ ዘመኑን የሚመጥን ብቃት ያለው የሰው ኃይል ማፍራት የሚያስችል አሠራር ዘርግቶ እየተገበረ መሆኑን ተናግረዋል።

በሰላም ማስከበር ሥራ ኢትዮጵያ ያላትን የካበተ ልምድ ከሌሎች አካላት አቅም ጋር በመደመር የበለጠ ውጤታማ ሥራ መሥራት እንደሚገባት መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የሠላም ማስከበሩ ሥራ በተሳካ ሁኔታ እንዲከናወን የሁሉም ባለድርሻ አካላት አጋርነት በተጠናከረ ሁኔታ መቀጠል እንዳለበትም ነው የተናገሩት።

ማዕከሉ ለሠላም ማስከበር ተልዕኮ አጋዥ የሆነ የሰው ኃይል ለማፍራት እየሰራ መሆኑን የገለጹት ደግሞ በዓለም አቀፍ ሠላም ማስከበር ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የሥልጠናና ትምህርት ዲን አቶ ከድር አባቡልጉ ናቸው።

ብቃት ያለው የሰው ኃይል ለማፍራት ለአኅጉራዊና ዓለም አቀፍ የሠላም ማስከበር ተልዕኮ መሳካት የሚደረገው አስተዋጽዖ ለማጠናከር የአጋር አካላት ሚና ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመዋል።

አጋር አካላት ኢንስቲትዩቱን በፋይናንስ፣ በቴክኒክና የተለያዩ ልምዶችን በማካፈል እያገዙ እንደሚገኙ ገልጸው ይህ ድጋፍ መጠናከር እንዳለበትም አስረድተዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.