Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮ – ጃፓን የቢዝነስ እና ኢንቨስትመንት ፎረም በአዲስ አበባ ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 28 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮ – ጃፓን የቢዝነስ እና ኢንቨስትመንት ፎረም በአዲስ አበባ ተካሄደ።

ፎረሙ በኢትዮጵያ ያሉ የንግድ እና ኢንቨስትመንት እድሎችን ለማስተዋወቅ ያለመ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመካከለኛው ምሥራቅ እስያ እና የፓሲፊክ ሀገራት ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር ገበየሁ ጋንጋ በመርሐ-ግብሩ ላይ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል፡፡

በንግግራቸውም ኢትዮጵያ በአፍሪካ ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት እና ሠፊ የመልማት ዐቅም ካላቸው ሀገራት አንዷ ናት ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከጃፓን ጋር የሁለትዮሽ ግንኙነቷን ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗንም አስምረውበታል፡፡

በኢትዮጵያ ያለውን ሠፊ የመልማት ዐቅም በተመለከተ ከጃፓን የቴክኖሎጂ ፈጠራ ውጤቶች ጋር ተደምሮ የሁለቱን ሀገራት ምጣኔ ሐብታዊ ግንኙነት ለማጠናከር ትልቅ አቅም እንደሚፈጥሩ አመላክተዋል፡፡

በጃፓን የኢትዮጵያ አምባሳደር ዳባ ደበሌ በበኩላቸው፥ ፎረሙ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት በተለያዩ መስኮች ከማጠናከር ባለፈ ኢትዮጵያ በግብርና፣ ቱሪዝም፣ ማምረቻው፣ ማዕድን እና አይ.ሲ.ቲ ዘርፎች ያላትን ዐቅም ለማሻሻል ዕድል እንደሚፈጥርላት አስረድተዋል።

በፎረሙ የኢንቨስትመንትና የንግድ ዕድሎች ፣ የውጭ ኢንቨስትመንት ማበረታቻዎች፣ ሕጎች እና ሥርዓቶች ላይ ገለጻ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.