Fana: At a Speed of Life!

መቐለ ዩኒቨርሲቲ ከ1 ሺህ በላይ አዲስ ተማሪዎችን መቀበል ጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 28 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) መቐለ ዩኒቨርሲቲ በትምህርት ሚኒስቴር የተመደቡለትን ከ1 ሺህ በላይ የተፈጥሮና የማህበረሰብ ሳይንስ አዲስ ተማሪዎችን መቀበል መጀመሩን አስታወቀ።

የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክተር ከሰተ ለገሰ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንደተናገሩት፥ ተቋሙ አዲስ ተማሪዎች እስከ ሕዳር 30 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ይቀበላል።

ተቋሙ የተማሪዎች ማደሪያ፣ የመማሪያ ክፍል፣ ግቢውን የማስዋብና ሌሎች ለመማር ማስተማሪ ስራ የሚያስፈልጉ መገልገያዎችን ቀደም ሲል ማመቻቸቱን ገልጸዋል።

በዚህም ዩኒቨርሲቲው አዲሶቹን ተማሪዎች በጥራትና በብቃት አሰልጥኖ ለማውጣት አበክሮ እንደሚሰራም አስታውቀዋል።

አዲስ ገቢ ተማሪዎች በበኩላቸው፥ በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው የሰላም፣ ፍቅርና አንድነትና ተምሳሌት ለመሆን የድርሻቸውን እንደሚወጣ ተናግረዋል።

መቐለ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ከ2 ሺህ በላይ ተማሪዎች በቅርቡ ማስመረቁ ይታወሳል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.