Fana: At a Speed of Life!

ካናዳ ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ስኬታማነት ድጋፍ እንደምታደርግ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ሥራዎች ስኬታማ እንዲሆኑ ካናዳ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ ታደርጋለች ሲሉ በኢትዮጵያ የሀገሪቱ አምባሳደር ጆሿ ታባህ ገለጹ፡፡

የሰላም ሚኒስትር ብናልፍ አንዷለም በኢትዮጵያ ከካናዳ አምባሳደር ጆሿ ታባህ ጋር በሁለትዮሽ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በአዲስ አበባ ተወያተዋል፡፡

በውይይታቸው ወቅትም አምባሳደር ጆሿ ታባህ እንደገለጹት÷ በኢትዮጵያ ሀገራዊ የሰላም ግንባታ ሂደት እና በግጭት ቅድመ ማስንጠቀቂያና ምላሽ ሥርዓት ዘርፍ የካናዳ መንግስት ድጋፍ ያደርጋል፡፡

በተጨማሪም የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ሥራዎች ስኬታማ እንዲሆኑ የካናዳ መንግሥት አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ ያደርጋል ማለታቸውን የሰላም ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.