Fana: At a Speed of Life!

ህግና ህገ መንግስቱ የተቋቋመው የህዝቦችን እኩልነት ለማረጋገጥ ነው – ም/አፈ ጉባኤ ኤሊያስ ኡመታ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ህግና ህገ መንግስቱ የተቋቋመው የህዝቦችን እኩልነት ለማረጋገጥ ነው ሲሉ የጨፌ ኦሮሚያ ም/አፈ ጉባኤ ኤሊያስ ኡመታ ተናገሩ፡፡

18ኛው የብሔር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀንን በማስመልከት በኦሮሚያ ክልል ደረጃ በምስራቅ ሐረርጌ ዞን እና በማያ ከተማ የፓናል ውይይት እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በፓናሉም አንድነት ከማስረፅና ጠብቆ ማስቀጠል ላይ ጠንከር ያሉ ሀሳቦች ተነስተው በሰፊው ዉይይት እየተደረገባቸው ሲሆን አባ ገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና በየደረጃው ያሉ አመራሮች ተሳትፈውበታል፡፡

በመድረኩ የተገኙት የጨፌ ኦሮሚያ ምክትል አፈ ጉባኤ ኤሊያስ ኡመታ የህገ መንግሥቱ መሠረት ብሔር፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች እንደመሆናቸው መጠን ህጉ የእኩልነት መብት የሚጠበቅበት፣ ወንድማማችነት የሚንፀባረቅበት እና የምንከባበርበት ነው ብለዋል፡፡

የወንድማማችነት እሴታችንን በመጠበቅ ህዝባችን ከሌሎች ህዝቦች ጋር ያለውን ህብረት በማጠናከር ኢትዮጵያ የጀመረችውን ልማት ከግብ ማድረስ ይገባል ሲሉም አስገንዝበዋል፡፡

በተጨማሪም በፓናሉ ላይ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ ምሁራን ጥናታዊ ፁሁፎችን አቅርበው ውይይት ተካሂዷበታል።

በቲያ ኑሬ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.