Fana: At a Speed of Life!

አቶ አገኘሁ ተሻገር በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል፡፡

የፋና ብሮድካስቲንግ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አድማሱ ዳምጠውን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች በክልሉ በዑራ ወረዳ በአምባ 1 ቀበሌ በሌማት ትሩፋት እየተከናወኑ የሚገኙ የእንቁላል፣ የዶሮ፣ የንብ መንደር፣ የወተት መንደር እና ሌሎች የልማት ስራዎችን ተመልክተዋል።

አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት÷ በክልሉ እየተሰሩ ያሉ የሌማት ትሩፋት ስራዎች የአርሶ አደሩን የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ የጎላ ፋይዳ እንዳላቸው መግለጻቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በክልሉ ያለውን የተፈጥሮ ፀጋ እና እምቅ አቅም በአግባቡ በመጠቀም በሌማት ትሩፋት ተጨባጭ አበረታች ስራዎች መከናወናቸውንም ነው የገለጹት፡፡

የህብረተሰቡን ኑሮ ከመለወጥ ባለፈ በኢኮኖሚ የበለፀገ አካባቢን በመፍጠር ረገድ ወሳኝ ምዕራፍ በመሆኑ የተጀመሩ የሌማት ትሩፋት ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም አንስተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.