Fana: At a Speed of Life!

ሙስናን በአስተሳሰብና በተግባር በመፋለም ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በጋራ እንስራ – ከንቲባ አዳነች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሙስናን በአስተሳሰብና በተግባር በመፋለም የሁላችንንም ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በጋራ እንስራ ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጥሪ አቀረቡ፡፡

“ሙስና የጋራ ጠላታችን ነው፤ በጋራ እንታገለው” በሚል መሪ ቃል ከተማ አቀፍ የጸረ ሙስና ንቅናቄ መርሐ ግብር በአዲስ አበባ ከተማ ተካሂዷል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት÷ ሙስናን ተፋልሞ የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ በተግባር የተለወጠ፣ አርዓያ የሚሆን፣ ለገባው ቃል የሚታመንና ለዓላማና ለሌጋሲ የሚሰራ አመራር ያስፈልጋል፡፡

ሙስና እና ብልሹ አሰራርን ታግሎ ለማሸነፍ ሙስናን የሚጸየፍ ማኅበረሰብ መገንባትም ወሳኝ ስራ መሆኑንም አስገንዝበዋል።

ሀብታችንን በእውቀት በማስተዳደር፣ አገልግሎት አሰጣጣችንን በማዘመን እና ተጠያቂነትን በማስፈን ሙስናን በአስተሳሰብና በተግባር በመፋለም የሁላችንንም ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በጋራ እንስራ ሲሉም በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.