Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ ተሞክሮ ለተለያዩ ሀገራት ተነሳሽነትን ፈጥሯል – ቢልለኔ ስዩም

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ ተሞክሮ ለተለያዩ ሀገራት ተነሳሽነት መፍጠሩን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ ቢልለኔ ሥዩም ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ባለፈው ሣምንት ሦስት ሀገራትን ጎብኝተዋል፡፡

በዚህም በኦስትሪያ በነበራቸው ቆይታም አመርቂ ተሳትፎ እንደነበራቸው ያነሱት ኃላፊዋ፥ በቼክ ሪፐብሊክ ጉብኝት ማድረጋቸውም ተነስቷል፡፡

ቀደም ብለው የቼክ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢትዮጵያ ተገኝተው እንደነበር ይታወሳል፡፡

በዚያን ወቅትም ጠቅላይ ሚኒስትሮቹ በሀገራዊ እና ሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ምክክር ማድረጋቸውም የሚታወስ ነው፡፡

ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በቼክ ሪፐብሊክ በነበራቸው ቆይታ በዋናነት በቱሪዝምና በግብርና ዘርፎች በጋራ ለመስራት ስምምነት መደረሱም ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም የአየር ኃይልን ለማጠናከርና አብሮ ለመስራትም ምክክር የተደረገ ሲሆን፥ ከዚህ ጋር ተያይዞ የአውሮፕላን ጥገናና እድሳት ላይ የልምድ ልውውጥ ለማድረግም ተስማምተዋል ነው የተባለው፡፡

መሪዎቹ በሰጡት የጋራ መግለጫ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ ያላትን የባህል እሴቶች ለማስተዋወቅ በትብብር ለመስራት መግባባት ላይ መደረሱን ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም በተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች ባደረጉት ቆይታ በተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ (ኮፕ28) ተሳትፈዋል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞም ኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ ስኬቶቿን፣ የምግብ ዋስትና እና ከታዳሽ ኃይል ጋር ተያይዞ እየተጓዘችባቸው የሚገኙ ሁኔታዎችን በመካነ ርዕይ ተሰድሮ ለዕይታ ቀርቧልም ነው የተባለው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉባዔው ላይ ያደረጉት ንግግርም የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ ተግባር ላይ ያተኮረ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በኢትዮጵያ ባለፉት አምስት ዓመታት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) አነሳሽነት የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብሩ በተግባር እየተካሄደ እንደቆየ ማንሳታቸው ተገልጿል፡፡

የሌማት ትሩፋት መርሐ ግብርም ከአረንጓዴ አሻራ ጋር የተያያዘ እንደሆነ እና ታዳሽ ኃይል መጠቀም በአረንጓዴ ልማት ላይ ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንዳለውም አንስተዋል ነው የተባለው በጉባዔው፡፡

በዚህም የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ ተሞክሮ በተለያዩ ሀገራት ተነሳሽነትን መፍጠሩን ኃላፊዋ አንስተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች በነበራቸው ቆይታ ከጉባኤው ጎን ለጎን ከተለያዩ መሪዎች ጋር ምክክር ማድረጋውም ነው የተገለጸው፡፡

በመሰረት አወቀ

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.