Fana: At a Speed of Life!

መዲናችን አካታችነቷን የምታሳየው አካል ጉዳተኞችን ጭምር ተጠቃሚ በማድረግ ነው – ከንቲባ አዳነች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) መዲናችን አካታችነቷና የብልፅግና ተምሳሌትነቷን የምታሳየው አካል ጉዳተኞችን ጭምር ተጠቃሚ በማድረግ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ 31 ኛውን ዓለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች ቀን ምክንያት በማድረግ አካታችነትን የሚያበረታታ ፕሮግራም “አብርሆት ለልበ ብርሀኖች” በሚል መሪ ሀሳብ መካሄዱን ገልጸዋል።

በዚህም ለዓይነ ስውራን የማንበብ፣ የምርምር ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር እና አካታችነትን የሚያበረታታ ኘሮግራም መካሄዱን አመልክተዋል’

አካል ጉዳተኝነት አለመቻል ሳይሆን በውስጣቸው፤ ያሉ እምቅ ችሎታዎችን በጥበብ ለማውጣት ዕድልና ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር የሚጠይቅ እንደሆነም አስረድተዋል።

አዲስ አበባ አካታችነቷና የብልፅግና ተምሳሌትነቷን የምታሳየው አካል ጉዳተኞችን ጭምር ተጠቃሚ በማድረግ እንደሆነ ገልጸው፤ መዲናዋ ለአካል ጉዳተኞች ምቹ እንድትሆን የሚሰራ መሆኑን በመልዕክታቸው አረጋግጠዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.