Fana: At a Speed of Life!

ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ የሲዳማ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ አሳሰበ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በክልልም ሆነ በሀገር ደረጃ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ የሲዳማ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ አሳስቧል፡፡

በሰላም ሚኒስቴር አስተባባሪነት በሲዳማና ደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች ድንበር አካባቢ የህዝብ ለህዝብ ምክክር መድረክ በሀዋሳ ከተማ ተካሂዷል።

የሲዳማ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አለማየሁ አሰፋ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት÷ የተገኘው ሰላም ቀጣይነት እንዲኖረው ሁሉም በአግባቡ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።

የሰላም ጉዳይ የሁሉም ጉዳይ ስለመሆኑ ሁሉም ህብረተሰብና ባለድርሻ አካላት በትኩረት በመስራት የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ማጠናከር እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ወገኔ ብዙነህ በበኩላቸው÷ በህዝብ መካከል የሚነሱ ግጭቶችን በባህላዊ መንገድ ለመፍታት የህዝቡ ሚና የላቀ መሆኑን አንስተዋል።

ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ለማስቻል ሁሉም ዜጋ የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ አስተላልፈዋል።

በተመስገን ቡልቡሎ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.