Fana: At a Speed of Life!

ምክር ቤቱ የአንድ ዳኛ ስንብት አስመልክቶ የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መራ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከዳኞች አስተዳዳር ጉባዔ ለምክር ቤቱ የቀረበውን የአንድ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኛ ስንብት አስመልክቶ የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መራ።

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 7ኛ መደበኛ ጉባዔ ተካሂዷል።

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኛ ስንብትን በተመለከተ በቀረበው አጀንዳ ላይ የተወያየው ምክር ቤቱ የቀረበለትን የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ ለህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መርቷል።

ምክር ቤቱ ከዳኞች አስተዳዳር ጉባዔ የቀረበውን የዳኛ ስንብት ውሳኔ ሀሳብ ረቂቅ ውሳኔ ቁጥር 1/2016 ሆኖ ለህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እንዲመራ በ3 ድምጸ ጻቅቦ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን እንደገና ለማቋቋም የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 1308/2016 ሆኖ በሙሉ ድምጽ ጸድቋል፡፡

በተጨማሪም÷ ምክር ቤቱ የአፍሪካ መድሃኒቶች ኤጄንሲ ለማቋቋም የተደረገውን ስምምነት ማጽደቂያ ረቂቅ አዋጅን ለመደንገግ ያቀረበው ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 1309/2016 ሆኖ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.