የአሜሪካ ወታደራዊ አውሮፕላን በምዕራብ ጃፓን መከስከሱ ተሰማ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አንድ የአሜሪካ ወታደራዊ አውሮፕላን በምዕራብ ጃፓን ያኩሺማ ደሴት ባሕር ዳርቻ መከስከሱ ተሰማ፡፡
ሁኔታውን ተከትሎ የጃፓን የባሕር ጠረፍ ጠባቂዎች ወደ ቦታው የቅኝት መርከቦችን እና አውሮፕላኖችን እንደላኩ ዲፌንስ ብሎግ ዘግቧል፡፡
የጃፓን መከላከያ ሚኒስቴር ምንጮች እንደገለጹት ÷ “ሲቪ-22 ኦስፕሬይ” በመባል የሚታወቀው አውሮፕላን ከመከስከሱ ቀደም ብሎ ጃፓን በሚገኘው የአሜሪካው ዮኮታ የጦር ሰፈር ሥምንት ሰዎችን አሳፍሮ ነበር፡፡
በቀጣናው የአሜሪካ ጦር ኃይሎች ቃል አቀባይ ስለ ተፈጠረው ሁኔታ መረጃ እየሰበሰቡ መሆኑን ተናግረዋል።