የመንግሥት ተሽከርካሪዎችን የነዳጅ ፍጆታ የሚቆጣጠር ሥርዓት ሊተገበር ነው
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የመንግሥትን ተሽከርካሪዎች የነዳጅ ፍጆታን የሚቆጣጠር ሥርዓት ሊተገበር መሆኑ ተገለጸ።
የመንግሥት ንብረትና ግዢ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሐጂ ኢብሳ፥ ሥርዓቱ ተገቢ ያልሆነ የተሽከርካሪዎችን እንቅስቃሴ በመገደብ የነዳጅ ፍጆታቸውን ለመቆጠብ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ተግባራዊ የሚያደርግ ነው ብለዋል፡፡
ቴክኖሎጂው በመጀመሪያ ሙከራ ደረጃ በ10 የፌደራል ተቋማት እንዲተገበር ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውንም ተናግረዋል፡፡
በሂደት በ169ኙ የፌደራል ተቋማት እንደሚተገበርም ነው ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ የገለጹት፡፡
አቶ ሐጂ ኢብሳ ከዚህ በፊት በተዘረጋው የኤሌክትሮኒክ ግዢ ሥርዓት ውጤት ማስመዝገብ እንደተቻለ ጠቁመዋል፡፡
አዲሱ ቴክኖሎጂ የመንግሥትን ሐብት ከምዝበራ ይታደጋል የሚል ተሥፋ ከወዲሁ ተጥሎበታል፡፡
በአፈወርቅ እያዩ