Fana: At a Speed of Life!

ኤሎን መስክ ጋዛን እንዲጎበኝ በሃማስ ግብዣ ቀረበለት

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለማችን ቢሊየነር ኤሎን መስክ ጋዛን እንዲጎበኝ በሃማስ ግብዣ ቀረበለት፡፡

በሃማስ ታጣቂ ቡድን ውስጥ ከፍተኛ ሥልጣን ያላቸው ኦሳማ ሐምዳን ግብዣውን ያቀረቡት ኤሎን መስክ በእስራዔል ያደረገውን ጉብኝት ተከትሎ መሆኑን አውት ሉክ አስነብቧል፡፡

ኦሳማ ሐምዳን በቤሩት በሠጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ÷ ኤሎን መስክ በስሚ ስሚ ሳይሆን እራሱ በአካል ተገኝቶ በጋዛ ሕዝብ ላይ የደረሰውን እልቂትና የቦንብ ጥቃት ውድመት እንዲመለከት እጋብዛለሁ ብለዋል።

በትናንትናው ዕለት በፈረንጆቹ ጥቅምት ሰባት ሃማስ በእስራዔል ላይ ባደረሰው ድንገተኛ ጥቃት ከፍተኛ ጉዳት ያስተናገደችውን እና የ1 ሺህ 200 ንፁሐን ሕይወት የተቀጠፈባትን መንደር ከእስራዔሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ ጋር በመሆን ጎብኝተዋል፡፡

ኤሎን መስክ እስራዔል በጋዛ ላይ የምትወስደውን እርምጃ ይደግፋል የሚሉ መረጃዎችም ሲሰሙ ቆይተዋል፡፡

በእርግጥም የቢሊየነሩ ንብረት የሆነው ስታር ሊንክ ኩባንያ ያለ እስራዔል ፈቃድ የበይነ መረብ አገልግሎት ለጋዛ ላለመስጠት መስማማቱን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

የኤክስ ማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ ባለቤት የሆነው ኤሎን መስክ ፀረ ሴማዊ ወይም ፀረ-አይሁድ ልጥፎችን በቸልታ ይመለከታል የሚል ስሞታ ከእስራዔል ወገን ሲቀርብበት መቆየቱን ሬውተርስ አስታውሷል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.