Fana: At a Speed of Life!

ዕሴት የተጨመረባቸውን ምርቶች ወደ ውጭ መላክ መጀመራቸውን ማዕድን አቅራቢዎች ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዕሴት የተጨመረባቸው እና ያለቀላቸውን ምርቶች ወደ ውጭ ሀገር መላክ መጀመራቸውን ማዕድን አቅራቢዎች ገልጸዋል፡፡

በየዓመቱ የሚዘጋጀው የማዕድን ኤክስፖ በሚሊኒየም አዳራሽ ተዘጋጅቷል፡፡

በኤክስፖው የተለያዩ የማዕድን አቅራቢዎች ምርቶቻቸውን ያቀረቡ ሲሆን ዕሴት የተጨመረባቸውና ተሰርተው ያለቁ ማዕድናትን ወደ ውጭ ሀገር መላክ መጀመራቸውን ገልጸዋል፡፡

በዚህም ወደ ህንድ፣ ቻይና እና ሌሎች ሀገራት እየላኩ እንደሆነ ነው የተናገሩት ፡፡

ለስራቸው መሳለጥ መሟላት ያለባቸው የሰለጠነ የሰው ሃይል፣ የማሽን ዕጥረትና መሰል ችግሮች ቢቀረፉ የተሻለ ውጤት ማምጣት እንደሚቻልም ጠቁመዋል ፡፡

የማዕድን ሚኒስትር ዴኤታ ሚሊዮን ማቲዎስ በበኩላቸው፥ በቀጣይ በምርቶች ላይ ዕሴትን ጨምሮ ለመላክ የሚያስፈልጉ ማሽኖችን ለማስገባት በፋይናንስ፣ በክህሎት እንዲሁም የገበያ ትስስር መፍጠር ላይ መንግስት በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

ለጌጣጌጥ የሚሆኑ ማዕድናትን ዕሴት ጨምሮ ወደ ውጭ የመላክ ስራ ለመስራት ከጌጣጌጥና ማዕድናት ማህበር ጋር በጋራ እየሰራን ነውም ብለዋል፡፡

በቀጣይ ኢትዮጵያ በዘርፉ ሰፊ ስራ እንደሚጠብቃት ያነሱት ሚኒስትር ዴኤታው የምርምር ስራዎችም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አንስተዋል፡፡

በፈትያ አብደላ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.