በአማራ ክልል ባለሐብቶች ከ63 ሺህ ለሚበልጡ ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል መፍጠራቸው ተገለጸ
አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 12 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ሥራ የጀመሩ ባለሐብቶች ከ63 ሺህ ለሚበልጡ ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል መፍጠራቸው ተገለጸ፡፡
ባለሐብቶቹ በ2015 ዓ.ም 487 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ካፒታል አስመዝግበው የኢንቨስትመንት ፈቃድ በማውጣት የተሰማሩ ናቸው ተብሏል።
በ401 ኢንዱስትሪዎቻቸውም ከውጭ ሀገር ሲገቡ የነበሩ ምርቶችን በ78 ዓይነት ተኪ ምርቶች በማምረት የውጭ ምንዛሬ ማዳን መቻላቸው ተጠቁሟል፡፡
38ቱ ኢንዱስትሪዎች ደግሞ ምርታቸውን ወደ ውጭ በመላክ 127 ሚሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማስገኘታቸው ተገልጿል፡፡
ከ400 በላይ ኢንዱስትሪዎች በግንባታ ላይ እንደሚገኙም ተነግሯል፡፡
የልማት ፈቃድ ወስደው በማያለሙት ባለሐብቶች ላይም ክትትል እየተደረገ አስፈላጊው የማስተካከያ እርምጃ ይወሰዳል መባሉን አሚኮ ዘግቧል፡፡