Fana: At a Speed of Life!

በ3 ወራት ከውጭ በተላከ ገንዘብ ከ1 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ መገኝቱ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በመጀመሪያው ሩብ ዓመት ከውጭ ሀገራት ወደ ኢትዮጵያ ከተላከ ገንዘብ (ሬሚታንስ) ከ1 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ እንዲገኝ ድጋፍ መደረጉ ተገለጸ።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና ሠላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን የ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ገምግሟል፡፡

ከቆንስላ አገልግሎቶች እና ከኅንጻ ኪራይ ከ341 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰብ መቻሉም በግምገማው ወቅት ተጠቅሷል፡፡

1 ሺህ 67 በውጭ ሀገር የመብት ጥሰት የደረሰባቸው ዜጎችም ካሳ እንዲያገኙ መደረጉም ተገልጿል፡፡

በሕገ ወጥ መንገድ ወደ ውጭ ሀገራት የተጓዙ 10 ሺህ 672 ዜጎች ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ መደረጉንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.