Fana: At a Speed of Life!

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከለሚ እንጀራ ፋብሪካ ጋር ለመሥራት ፍላጎት እንዳለው ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) የለሚ እንጀራ ፋብሪካን ጎብኝተዋል፡፡

ከጉብኝታቸው በኋላም ለለሚ እንጀራ ፋብሪካ የተሻለ የገበያ ትስስር መፍጠር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በቀጣይ ከለሚ እንጀራ ፋብሪካ ጋር በቅርበት አብሮ ለመስራት እንደሚፈልግ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) መግለጻቸውን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በበኩላቸው÷ ፋብሪካው በሙሉ ዐቅሙ እንዲያመርት ጠንካራ የስራ ባህል ማዳበር፣ አስተዳደሩን ማጠናከር እና የተሻለ የገበያ ትስስር ለመፍጠር እንሰራለን ብለዋል፡፡

ፋብሪካው አዲስ እና ለበርካታ እናቶች የስራ እድል የፈጠረ በመሆኑ ውጤታማ እንዲሆን በቅርበት ክትትል እናደርጋለንም ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.