ከ284 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ284 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዙን የኢፌዴሪ ጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
224 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር ገቢ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች እና 59 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር ወጪ ዕቃዎች በድምሩ 284 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚያወጡ የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን በተለያዩ ቅርንጫፎች ተይዘዋል።
ከተያዙት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መካከል አልባሳት፣ ነዳጅ፣ የቁም እንስሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ መድሀኒት፣ ተሽከርካሪዎች፣ የመዋቢያ እቃዎች፣ የጦር መሳሪያዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች፣ የምግብ ዘይት እና የተለያዩ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል ተብሏል፡፡
በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ የገቢ እና የወጪ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር ረገድ ድሬዳዋ፣ አዋሽ እና ሞያሌ ቅርንጫፍ ጽኅፈት ቤቶች ቀዳሚውን ሥፍራ መያዛቸውንም ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡