Fana: At a Speed of Life!

ህንድ የሰብዓዊ እርዳታ ወደ ጋዛ ላከች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ህንድ የንፁሃን ዜጎችን ህይዎት ይታደጋል ያለችውን ሁለተኛ ዙር የሰብዓዊ እርዳታ ወደ ጋዛ መላኳን አስታውቃለች፡፡

መድሃኒት እና የአደጋ መከላከያ ቁሳቁሶችን የያዘው ሁለተኛው ዙር የሰብዓዊ እርዳታ ለግብፅ ቀይ ጨረቃ መድረሱም ተመላክቷል፡፡

የህንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሱራህማንያም ጃይሻንካር÷ ኒው ዴልሂ ለፍልስጤማውያን የምታደርገውን የሰብዓዊ ድጋፍ አጠናክራ ትቀጥላለች ብለዋል፡፡

ህንድ ከአንድ ወራት በፊት በጋዛ መድሃኒቶችን፣ የቀዶ ህክምና መሳሪያዎችን፣ መጠለያ ድንኳኖችን፣ የመኝታ ከረጢቶችን፣ የንፅህና መገልገያዎች እና የውሃ ማጣሪያዎችን ያከተተ የመጀመሪያ ዙር የሰብዓዊ ድጋፍ ማድረጓ ይታወሳል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ መንግስት እየተተኮሱ ባሉ ሚሳኤሎች በሚሞቱ ንፁሃን ፍልስጤማውያን ሃዘኑን ሲገልፅ የቆየ ሲሆን እየተካሄደ ያለው የእስራኤል እና ሃማስ ጦርነት እንደሚያሳስበው መግለፁን አር ቲ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.