Fana: At a Speed of Life!

ለአፍሪካ የኢንዱስትሪ ዕድገት የቴክኖሎጂ ፈጠራ እና የሰው ሐብት ወሳኝ ናቸው – ጥናት

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ ዘላቂ የኢንዱስትሪ ዕድገትን ዕውን ለማድረግ የቴክኖሎጂ ፈጠራን ከሰው ሐብት ልማት ጋር ማጣጣም እንደሚያስፈልግ ጥናት ውጤት አመላከተ፡፡

“በአፍሪካ ዘላቂ የኢንዱስትሪ ልማትን ዕውን ለማድረግ አስቻይ ጉዳዮች” በሚል መሪ ሐሳብ የዚህ ዓመት የአፍሪካ የምጣኔ-ሐብት ጉባዔ በአዲስ አበባ ለሦስት ቀናት ተካሂዷል።

በጉባዔው ላይም ተመራማሪዎች በምጣኔ ሐብት ዘርፍ የአፍሪካን መፃዒ ዕድል የሚያመላክቱ የጥናት ውጤቶቻቸውን አቅርበዋል፡፡

በጥናቶቹም÷ ከፈረንጆቹ 1996 እስከ 2021 ድረስ ከ32 የአፍሪካ ሀገራት በቴክኖሎጂ ፈጠራ፣ በሰው ሐብት ልማት፣ የኢንዱስትሪ ምርታማነት እና ተወዳዳሪነት ላይ ያሉ ተግዳሮቶችና ዐቅሞች ተዳስሰዋል፡፡

ከበለጸጉ ሀገራት እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር በተለይ በቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ በትብብር መሥራት እንደሚገባም ነው የጥናቶቹ ውጤት ያመላከተው፡፡

የአፍሪካ ልማት ባንክ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን እና የተመድ የልማት ፕሮግራም በጥምረት ባዘጋጁት ጉባዔ ላይ ÷ የኢትዮጵያ ፖሊሲ አውጪዎች፣ ተመራማሪዎች እንዲሁም ወጣጦች ተሳትፈዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.