በመዲናዋ ባለፉት 4 ወራት ለ50 ሺህ በላይ ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል መፈጠሩ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት አራት ወራት ለ50 ሺህ 569 ሥራ ፈላጊዎች ቋሚ የሥራ እድል መፍጠር መቻሉን በአዲስ አበባ ከተማ የሥራ፣ ኢንተርፕራዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ አስታውቋል፡፡
የቢሮው የዘርፍ አመራሮች፣ ከክፍለ ከተማ ምክትል ጽ/ቤት ኃላፊዎችና ምክትል ሥራ አስፈፃሚዎች ጋር የአራት ወራት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን ገምግመዋል፡፡
በዚህም በ2016 በጀት ዓመት አራት ወራ ለ50 ሺህ 569 ሥራ ፈላጊዎች ቋሚ የስራ እድል መፍጠር መቻሉ ተገልጿል፡፡
ግምገማው ባለፉት ወራት የገጠሙ ችግሮች ነቅሶ በማውጣት ጥራትንና ፍትሐዊነትን መሰረት ያደረገ ሥራ መስራት እንደሚያስችል የቢሮው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከሥራው ጋር በቅርበት እስከ ወረዳ ድረስ በመውረድ በጋራ ሰርቶ ውጤታማ የሥራ ዕድል ፈጠራ፣ ፍትሃዊ የመስሪያ ቦታ አሰጣጥና የኢንዱስትሪ ምርታማነትን ማሳደግ እንደሚገባም ተጠቅሷል፡፡