በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ፍሰትን ማበረታት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስትር ዴዔታ ሰመሪታ ሰዋሰው በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት አማራጮች ዋሥትና ኤጀንሲ ም/ፕሬዚዳንት ጁነዲን ከማል ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም÷ በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ፍሰትን ማበረታታት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ በትኩረት መክረዋል፡፡
መንግስት የኢትዮጵያን የምጣኔ ሐብት አወቃቀር ከመንግሥት አላቆ ወደ ግሉ ዘርፍ ለማዞር እየሠራ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
ለውጡን ለማፋጠን የተቀናጀ የልማት አጋሮች ድጋፍ እንደሚያስፈልግም ወይዘሮ ሰመሪታ ሰዋሰው መናገራቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያ ከኤጀንሲው እያገኘች ላለው ድጋፍ አመሥግነው ÷ የኢትዮጵያ መንግስት የማክሮ ኢኮኖሚ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ እያካሄደ ስላለው የምጣኔ ሐብት ማሻሻያ ገለጻ አድርገዋል።