ዴቪድ ካሜሩን የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 3 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሩን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው መሾማቸው ተሰማ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ የካቢኔ ሹም ሽር አካሂደዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሃገር ውስጥ ሚኒስትር ሱዌላ ብሬቨርማንን ከስልጣን ማንሳታቸውን ቢቢሲ በዘገባው አስነብቧል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት ጄምስ ክሌቨርሊን በእርሳቸው ምትክ መተካታቸውንም ነው ዘገባው ያስነበበው።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት ዴቪድ ካሜሩን፥ ከስድስት አመታት በኋላ በከፍተኛ የመንግስት የሃላፊነት ቦታ ወደ ስልጣን ተመልሰዋል።
ካሜሩን እንግሊዝን ከፈረንጆቹ 2010 እስከ 2016 ድረስ በጠቅላይ ሚኒስትርነት ማገልገላቸው ይታወሳል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!