በሕንድ በግንባታ ላይ ያለ የመተላለፊያ ዋሻ ተደርምሶ ከ30 በላይ ሰራተኞች አደጋ ላይ መውደቃቸው ተሰማ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሕንድ ሂማሊያ ግዛት በተከሰተ የመሬት መንሸራተት በግንባታ ላይ ያለ የመተላለፊያ መንገድ ዋሻ በመደርመሱ ከ30 በላይ የሚሆኑ የግንባታ ሰራተኞች አደጋ ውስጥ መውደቃቸው ተሰምቷል፡፡
የተደረመሰው የዋሻው ክፍልም ከዋሻው መግቢያ 200 ሜትር ርቆ እንደሚገኝ ስካይ ኒውስ ዘግቧል፡፡
ዋሻው የተደረመሰባቸው የግንባታሰራተኞች በህይወት እንዳሉ የሚያሳይ መልዕክት መላካቸው የተገለጸ ሲሆን የሀገሪቱ የአደጋ መከላከል ሰራተኞችና በጎ አድራጊዎች ህይዎታቸውን ለማትረፍ እየተረባረቡ ነው ተብሏል፡፡
የአደጋውን ሰለባዎችን ህይወት ለመታደግ ጥረት እየተደረገ ሲሆን የነፍስ አድን ስራው ጊዜ ሊወስድ እንደሚችል ተጠቁሟል።
አደጋው የተከሰተበት የሰሜናዊ ህንድ ሰሜናዊ ሂማሊያ ግዛት ኡታራክሃንድ በሚባል የሚታወቅ ሲሆን አካባቢው ባለው በርካታ ሰው ሰራሽ የቅርስ ሀብት በየዓመቱ ከፍተኛ የሆነ የቱሪስት ፍሰት የሚያስተናግድ አካባቢ መሆኑ ተገልጿል።