Fana: At a Speed of Life!

በአይስላንድ ከእሳተ ገሞራ ስጋት ጋር ተያይዞ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታወጀ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 3 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አይስላንድ የእሳተ ገሞራ ሊፈነዳ ይችላል በሚል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀች።

በሃገሪቱ ደቡባዊ ምዕራብ ጠረፋማ አካባቢ የርዕደ መሬት ንቅናቄ መከሰቱን ተከትሎ እሳተ ገሞራ ሊፈነዳ ይችላል በሚል ስጋት ነዋሪዎች አካባቢያቸውን ለቀው እንዲወጡ የሃገሪቱ ባለስልጣናት አስጠንቅቀዋል።

የሃገሪቱ የሚቲዮሮሎጅ ጽህፈት ቤትም “እሳተ ገሞራ ሊከሰት የሚችልበት ዕድል” መኖሩን ገልጿል።

አሁን ላይ ከመሬት በታች ንቁ የሆነ ቅልጥ አለት በአካባቢው መኖሩን የጠቆመው ቢሮው ይህ በማንኛውም ሰአት ሊፈነዳ እንደሚችልም ነው ያስነጠቀቀው።

በጠረፋማዋ አነስተኛ ከተማ ግሪንዳቪክ መጠነኛ የሆነ እና ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱንም አስታውቋል።

ካለፈው አርብ ጀምሮ ወደ 800 የሚጠጉ መጠነኛ የመሬት ንቅናቄ እና ንዝረት መከሰቱም ነው የተጠቆመው።

አይስላንድ በተደጋጋሚ እሳተ ገሞራ የሚጎበኛት ሃገር ስትሆን ከፈረንጆቹ 2021 ጀምሮ በአመት አንድ ጊዜ የዚህ ክስተት ተጋላጭ መሆኗን ሲ ኤን ኤን አስነብቧል።

ለመጨረሻ ጊዜ የፈነዳው እሳተ ገሞራም ባለፈው ሃምሌ ወር ላይ መከሰቱንም ነው ዘገባው ያስታወሰው።

አይስላንድ በጣም ዝግጁ ወይም ንቁ የሆኑ (አክቲቭ ቮልካኖ) 32 እሳተ ገሞራዎች እንደሚገኙባትም መረጃው አመላክቷል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.