Fana: At a Speed of Life!

ትሬሲ ቻፕማን ከ35 ዓመት በፊት ያቀነቀነችው ሙዚቃ የዓመቱን ምርጥ ሽልማት አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ትሬሲ ቻፕማን ከ35 ዓመታት በፊት ባቀነቀነችው “ፋስት ካር” ሙዚቃ የዓመቱን ምርጥ የአሜሪካ የሀገረ-ሰብ ዘፈን ሽልማትን አሸነፈች፡፡

ትሬሲ ቻፕማንን ለአሸናፊነት ያበቃት ከ35 ዓመታት በፊት ያቀነቀነችው “ፋስት ካር” የሚለው የሀገረ-ሰብ ሙዚቃ መሆኑን ኒውዮርክ ታይምስ አስነብቧል፡፡

በፈረንጆቹ 1988 ላይ የተለቀቀው “ፋስት ካር” ሙዚቃ በአሜሪካ የሀገረ-ሰብ ሙዚቃዎች የደረጃ ሠንጠረዥ ታሪክ በቀዳሚነት የተቀመጠ መሆን የቻለ ነው፡፡

ትሬሲ ቻፕማን ÷ በዚህ ዘፈኗ ስለ “ፈጣን መኪና” ሳይሆን የምታነሳሳው ስለ ድሕነት እና ከድሕነት ለማምለጥ ስለምትጣጣር ምስኪን ሴት ታሪክ ነው፡፡

አሜሪካዊቷ ዘፋኝ “ፋስት ካር” የተሰኘው ዘፈኗን ራሷ “ዴቢዩት” ብላ በሰየመችው የመጀመሪያ አልበሟ ነው ያካተተችው፡፡

የ59 ዓመቷ ትሬሲ ቻፕማን ሽልማቱን ማሸነፍ የቻለች የመጀመሪያዋ ጥቁር አሜሪካዊት መሆን መቻሏን ሮሊንግ ስቶን የተሠኘው መጽሔት ይዞ በወጣው ፅሑፍ አጋርቷል።

ዘፈኑ ይበልጥ የገነነው በዌምብሌይ ስቴዲየም በኔልሰን ማንዴላ 70ኛ ዓመት የልደት ኮንሰርት ላይ ከቀረበ በኋላ መሆኑ ይነገራል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.